የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስና የፕሮግራሙ ዘላቂነት ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡
የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስና የፕሮግራሙ ዘላቂነት ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም
"ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጥ!!!!" በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ22ኛ ጊዜ የኤች አይቪ ቀን ተከበረ፡፡
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት ከማረጋገጥ አንጻር እየገጠመን ያለውን የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ ተግዳሮትን ከስረ-መሰረቱ መፍታትንና የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ ላይ እምርታዊ ለውጥ ማምጣትን በሁሉም ባለድርሻ አካላት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ የመሠራትን አስፈላጊነት ለማጉላት ነው (ዶ/ር ፋሲካ በለጠ)፡፡
በዓለም 630,000 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡ፣በአፍሪካ በ2023 ዓ.ም.390,000 ሰዎች ከኤድስ ጋር በተያያዙ በሽታዎች እንደሞቱና፣በየአመቱ 9,560 ሰዎች በኤድስ ምክንያት እንደሚሞቱ የኢ/ሕ/ጤ/ኢ መረጃ ያመላክታል ብለዋል፡፡
ለኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞች ከአለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪዎች ሲደረግ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ መቀነስና የፕሮግራሙ ዘላቂነት ላይ የራሱ የሆነ ተጽዕኖ ማሳደሩን አክለው ገልጸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments