"ለአረጋውያን ደህንነትና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ"
አዲስ አበባ፤ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ 34 ጊዜ "ለአረጋውያን ደህንነትና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ" በሚል መሪ ቃል የአረጋውያን ቀን ተከበረ፡፡
አረጋውያን በኢኮኖሚያዊ፣በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ፣ የጤና የትምህርትና የስልጠና አገልግሎቶችን የማግኘት፣ ምግብ ልብስና መጠለያ የመሳሰሉ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እና ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማግኘት መብቶች እንዳሏቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በትውልዶች መካከል ድልድይ ሆነው የሚያገለግሉ አረጋውያን ጤንነት፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው በአግባቡ ከተጠበቀ ጤናማ እና ተቀባይነት ያለው የትውልድ ሽግግር ሂደት መፍጠር ይቻላልም ተብሏል፡፤
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments