"ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

"ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ!!”

አዲስ አበባ፤ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም
የጸረ-ጾታዊ ጥቃት ቀን ንቅናቄ "ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ!!” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ለ34ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ ተከብሯል፡፡

የአልኮል እና የአደገኛ ሱስ ተጠቃሚ መሆን፣ ከማህበረሰቡ ያፈነገጠ ማንነት መኖር(antisocial personality disorder)የአደገኛ ፊልሞች(Pornography) ሱሰኛ መሆን፣ከአስተዳደግ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖር፣ የአቻ ግፊት፣ በቤተሰብ ውሰጥ ግልፅ የሆነ ውይይት አለመዳበር፣ማህበረሰቡ ፆታዊ ጥቃትን በተገቢው  መጠን ያለማውገዙ፣የኢኮኖሚ ዝቅጠት ለፆታዊ ጥቃት መከሰት እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚታዩት ችግሮች መሆናቸው በቀረበው ሰነድ ተነስቷል፡፡  

ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ህጻናት፣እድሜአቸው የገፉ ሰዎች፣የአእምሮ ህመምተኞች፣ የኢኮኖሚ ጥገኛ የሆኑ ሴቶች፣ እራሳቸውን መከላከል የማይችሉ የአካል ጉዳተኞች፣ወጣቶችና ባልቴቶች ወዘተ…በፆታዊ ጥቃት የበለጠ ተጎጂ የሆኑት የህብረተሰብ  ክፍል እንደሆኑ ተገለጸ፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments