ቅሬታና አቤቱታ አፈታትና የህግ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬ
መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ጠንካራ ተቋም መፍጠር ወሳኝ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ህዳር 25/2018 ዓ.ም
የቅሬታና አቤቱታ አፈታትና የህግ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በካሳ አከፋፈል ዙሪያ ለክፍለከተማ እና ወረዳ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
መልካም አስተዳደር ማለት ህብረተሰቡ የጣለውን ኃላፊነት እምንወጣበት ውሳኔዎቻችን ለተቋም እድገትና ለህዝብ ጥቅም የሚውልበት መንገድን የሚቀይስ ስርዓት ነው፡፡( የቅሬታና አቤቱታ አፈታትና የህግ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ታደሰ በዳዳ)
ጠንካራ ተቋማት መገንባት፣ህግና ፖሊሲ ማእቀፎችን ማሳደግ፣ሙስናን መከላከልና መቆጣጠር ፣ጠንካራ የግል ሴክተርና የሲቪክ ማህበራት መገንባት፣የህግ የበላይነትን ማጠናከር እና ጠንካራ የሚዲያ ተቋማት መገንባት መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚረዱን ስልቶች እንደሆኑ ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments