በ136 ማህበራት ለተደራጁ 680 ተጠቃሚዎች የዶ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በ136 ማህበራት ለተደራጁ 680 ተጠቃሚዎች የዶ/ሮና የኬጂ ድጋፍ ተደረገ፡፡

በ136 ማህበራት ለተደራጁ 680 ተጠቃሚዎች የዶ/ሮና የኬጂ ድጋፍ ተደረገ፡፡


አዲስ አበባ፤ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም


የልደታ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ሥር ካሉ 10 ወረዳዎች ለተመረጡ 680 ተጠቃሚዎች የዶሮ እና የኬጂ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የክፍለ ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ 50 ዶሮ መያዝ የሚችል 30 ኬጂ በፋሚሊ ቢዝነስ ለተደራጁ 136 ማህበራት የተሰራጨ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘውም 136 ኩንታል መኖ የተሰራጨ መሆኑን፣ በፋሚሊ ቢዝነስ የተደራጁት ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ከ10 ወረዳዎች የተውጣጡ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


ተጠቃሚዎች በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለኮሚሽኑ እና በስሩ ላለው መዋቅር እንዲሁም ለክፍለ ከተማው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ሌላው ያነጋገርናቸው በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጄኔ የከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን ከፍ ከማድረግ አንፃር የሌማት ትሩፋት እየተጫወተ ያለው ሚና ቀላል አለመሆኑን ገልፀውልናል፡፡


በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት ንቅናቄን ከግብ ለማድረስ በሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች ላይ በከፍተኛ ንቅናቄ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም የዶሮ እርባታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ ከባዮሴኩሪት አኳያ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ ያለበት መሆኑን አንስተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments