በአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬ የአርሶ አደር ልማት ቡድን ለስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የኢንቨስትመንት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25ቀን 2018 ዓ.ም
በአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬ የአርሶ አደር ልማት ቡድን ለስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች የኢንቨስትመንት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የስራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች በኢንቨስትመንት ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር በከተማው ውስጥ በከተማ ግብርና ላይ የተሰማሩትን አርሶ አደሮች በኢንቨስትመንት ቅኝት በመደገፍ እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን እንዲያገኙ መረጃ በመስጠት አርሶ አደሩ ከከተማ ግብርና ወደ ኢንቨስተርነት ኢንዲሸጋገሩ ማድረግ ነው፡፡ (የአርሶ አደር ልማት ቡድን መሪ ደግነሽ በደዊ)
የኢንቨስትመንት አመቺነት ማጥናት፣ ማስተዋወቅ፣ማስተባበር፣ማስፋፋት፣ምክርና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት፤የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ የንግድ ስራ ፈቃድ ማግኘት እንዲችሉ አግባብ ላለው አካል ማስተላለፍ፤የፋይናንስና የብድር አገልግሎት፣ የጥሬ እቃና የማምረቻ መሳሪያዎች የማግኘት እድልና የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች የሚሟሉበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት በባለሀባቶች፣ በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶችና በሌሎች ኢንቨስትመንትን በተመለከተ አግባብነት ባላቸው አካላት መካከል ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ፣ (የባለድርሻ አካላት ትስስር እና ቅንጅት)ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጡት ስልጣንና ተግባራት እንደሆኑ ሰነዱን ያቀረቡት አቶ መስፍን አብራርተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የልማት እንቅስቃሴ ሊደግፉ እና ሊያበረታቱ የሚችሉ የሰላም ሁኔታ የተረጋጋ መሆኑ፣ በቀላሉ መሰልጠን የሚችል የሰው ኃይል መኖሩ፡የተሻሻለ የመሠረተ ልማት አውታሮች ዝርጋታ መኖር፣ምቹ የገበያ ትስስር መኖር፣የአፍሪካ ዋና ከተማ ፣የአለም አቀፍ የዲኘሎማሲ ከተማ መሆን መቻሏ፣ እንደ አገር የኢኮኖሚ ሪፎርም መተግበር መቻሉ፣ የውጭ ባንኮች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ከተማዋን ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆን የአዲስ አበባ ከተማ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ ለተነሱትን ሀሳብና አስተያየት ምላሽ ተሰቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments