በሂሳብ አያያዝና በዘመናዊ ግብይት ሥራ አመራር ዙሪያ ለማህበራት ሥልጠና ተሰጠ።
በሂሳብ አያያዝና በዘመናዊ ግብይት ሥራ አመራር ዙሪያ ለማህበራት ሥልጠና ተሰጠ።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም
የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ የስራ ዘርፍ ለተሰማሩ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በሂሳብ አያያዝና በዘመናዊ ግብይት ሥራ አመራር ዙሪያ ሥልጠና ተሰጥቷል።
ሥልጠናው የተሰጠው ማዕከሉ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የህብረት ሥራ ማደራጃ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሲሆን ሠልጣኞች በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል።
የሥልጠናው ተሳታፊዎች ሥልጠናው ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው የወጪ ገቢ ደረሰኝ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ መሠጠቱ ለስራቸው ቀጣይነት ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ ይሄ ድጋፍና ክትትል ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።
የማዕከሉ የገበያ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሣራ ንጉሤ በሰጡት መልዕክት በሂሳብ ሰነድ አያያዝ ዙሪያ የሂሳብ መዝገብ ዝርጋታ ሌዠርና መሠል ሰነዶች ማዘጋጀት ለግብይቱ ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ በማጠቃለያው እነዚህንና መሠል ሥልጠናዎች የሚቀጥሉ መሆናቸውንና የገበያ ማረጋጋት ስራውን ለማስቀጠል የማህበራትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ማዕከሉ እንደሚሠራ በመግለፅ ሥልጠናው ተጠናቋል።
መረጃው፡- የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments