የደረሱ ሰብሎች  ወቅቱን  ጠብቀው  መሰብሰብ  ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የደረሱ ሰብሎች  ወቅቱን  ጠብቀው  መሰብሰብ  አለባቸው፡፡

የደረሱ ሰብሎች  ወቅቱን  ጠብቀው  መሰብሰብ  አለባቸው፡፡

አዲስ አበባ፤ህዳር  26/2018 ዓ.ም

በቦሌ ክፍለከተማ  ወረዳ 12 ሪፌንቲ  አካባቢ   የኮሚሽኑ  አጠቃላይ  አመራሮችና  ባለሙያዎችን  የአቅመ  ደካማ አርሶ  አደሮች    የደረሰ  ሰብል  ሰብስበዋል።

ም/ኮ ለማ ጸጋ (ዶ/ር) አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን  በርካታ ስራዎችን  እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡በመሆኑም  የንቅናቄው አላማ  አቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን ማገዝ  በመሆኑ ግብአት ከማመቻቸት እስከ  ሰብል  መሰብሰብ  ድረስ  ያለው  ሂደት ምርትና ምርታማነትን በማይጎዳ  መልኩ  በጥንቃቄ  ሰብስበን ለአርሶ አደሩ በማስረከባችን  ደስ ብሎናል ብለዋል፡፡

በእጸዋት ዳይሬክቶሬት የሰብል  ባለሙያ  ተስፋየ ኪዳነማርያም   ግማሽ ዩሪያና ግማሽ ዳፕ ማዳበሪያ  ተጠቅሞ  በመዝራት  እንደዚህ  ያማረ  ሰብል  ማየት ችለናል ካሉ በኋላ እንደኮሚሽናችን  ንቅናቄ ተደርጎ ከ300 በላይ  የሚሆኑ  ባለሙዎች  እና አመራሮች   መሳተፋቸውንም   ተናግረዋል፡፡
በእንስሳት ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት  አቶ ሀይሉ  ቀዲዳ  የግብአት  አመቻች ቡድን መሪ  ሰብሎች  ወቅታቸውን ጠብቀው  እንዲሰበሰቡና  አርሶ አደሮቹ የድካማቸውን ውጤት እንዲያገኙ  ድጋፍ  መደረጉ  የሚበረታታ ተግባር መሆኑንና  ሌላኛው  ጎን ደግሞ የኮሚሽኑ  ተልዕኮ በመሆኑ  በየዓመቱ  እንደሚቀጥል  ተናግረዋል፡፡

የቦሌ ክፍለከተማ  ግብርና ጽ/ቤት  ኃላፊ  ወ/ሮ ሰናይት  ዛሬ የተሰባሰብነው የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን የደረሱ ሰብል ለመሰብሰብ በመሆኑ የኮሚሽኑ አመራረሮችና ሰራተኞች በዚህ ልክ ወርደው ድጋፋቸውን ማሳየታቸው የሚበረታታ ስራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የማሳው ባለቤት የሆኑት አቶ ገመቹ አብዲ   በወቅቱ  ሰብላቸው በመሰብሰቡና  በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ  እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments