እንስሳት እና እጽዋት ሃብት ልማት ሥራ ዘርፍ ላይ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል
ከተማ ግብርና ከመደበኛ እንቅስቃሴው ጎን ለጎን ንቅናቄ ይፈልጋል።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ ቡድን መሪዎች ጋር በእንስሳት እና እጽዋት ሃብት ልማት ሥራ ዘርፍ ላይ የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።
የንቅናቄ ሰነዶቹን ለመወያያነት ያቀረቡት የዘርፉ ባለሙያዎች አቶ ዘላለም ታምራት እና አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያም ዘርፉን በንቅናቄ በማነቃቃት ምርትና ምርታማነቱን ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩት የክፍለ ከተማና የወረዳ ቡድን መሪዎች በዚህ ልክ መድረክ ተዘጋጅቶ መወያየታችን ይበረታታል ብለዋል።
የእንስሳት ሃብት ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጀኔ ግብርና ሰው ተኮር በመሆኑ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንፃር በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የእጽዋት ሃብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ ይህ ንቅናቄ በዋናነት ያስፈለገው በዘርፉ የተሰማራው የግብርና ቤተሰብ መነቃቃት ስላለበት መሆኑን ተናግረዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments