ለኢንዱስትሪ ግብአት እስከሚውልበት ደረጃ ለማድረስ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው፡፡
ለኢንዱስትሪ ግብአት እስከሚውልበት ደረጃ ለማድረስ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም
የሰርተፍኬሽን ኢንስፔክሽን ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ በባዮ ሴኩሪቲ፣ሀይጅንና ሳኒቴሽን እንዲሁም በቆዳና ሌጦ ጥራትና ቁጥጥር ዙሪያ ለክፍለከተማ ቡድን መሪዎችና ባለሙዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን ከወሰዳችሁ በኋላ ስራቸው መሬት ላይ ወርዶ መታየት እንዳለበትና ቆዳና ሌጦ ሀገራዊ እና አስፈላጊ ጉዳይ ከመሆኑ አንጻር ከሂደቱ ጀምሮ ወደሚፈለገው ለኢንዱስትሪ ግብአት እስከሚውልበት ደረጃ ለማድረስ ጥብቅ ቁጥጥርና ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው በመግቢያ ንግግራቸው አደራ ጭምር አስተላልፈዋል፡፡(ም/ኮ ፀጋ ለማ ዶ/ር)
ባዮ ሴኩሪቲ ስልታዊ ወይም የተቀናጀ ፖሊሲና ቁጥጥር ማእቀፍ ነው፡፡በመሆኑም ጎጅ ህዋሳትን ማስፋፋትን ለመከላከል እና ተላላፊ በሽታ አደጋን ለመቀነስ ያገለግላል ተብሏል፡፡
የጽንስ ሀሳብ ባዮ ሴኩሪቲ፣መዋቅራዊ ባዮ ሴኩሪቲ እና ተግባራዊ ባዮ ሴኩሪቲ ተብለው በሦስት መንገዶች የተከፈሉ ሲሆን እንሰሳት እንዴት ጤናማ እና ደህንነታቸው እንደሚጠበቅ ያስተምራሉ፡፡ ሰነዱን ያቀረቡት( ዶ/ር ሀብቶም)
የጤና ሁኔታቸው የማይታወቅ እንስሳት ጋር እንዳይገኛኙ መከላከል የመለያና የመከታታያ እርምጃዎች መኖራቸውን ማረጋገጥ እና የታመመውን እንስሳት በብቸኝነት ማገልገል ወሳኝ እንደሆነ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
የእንስሳት መጠናቸው ከፍተኛ በመሆኑ እና ከብክለት ጋር ንክኪ በመኖሩ ተገቢውን የባዮ ሴኩሪቲ እርምጃ ካልተተገበሩ የእንስሳት እርባታ ቦታዎች ለተላላፊ በሽታዎች ይጋለጣሉ፡፡(ዶ/ር ካሳየ)
እንደ (WOAH) ገለጻ ባዮ ሴኩሪቲ የእንስሳት በሽታዎች፣ኢንፌክሽኖች የማስፋፋት አደጋን ለመቀነስ የተቀየሰ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሆነም ጨምረው አብራርተዋል፡፡
457/2005 የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ሥርአት በተመለከተ የወጣ አዋጅ ሲሆን የእንስሳት እርባታና የቆዳ ምርትን የሚቆጣጠሩ አግባብነት ያላቸው ህጎች ናቸው ተብሏል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments