ኮምፖስት በማዕከሉ እየተመረተ ነው።
"በአንድ ድንጋይ ሁለት፣ ሦስት ወፍ"
ችግርን ወደ መልካም አጋጣሚ የመቀየር ውጤት!!
ኮምፖስት በማዕከሉ እየተመረተ ነው።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም
====
በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ማሳየት ተችሏል።
በማዕከሉ በተለይም ከዳልጋ ከብት ማድለብ እና ከወተት ከብት እርባታ ክላስተሮች የሚወጣው የእንስሳት እዳሪ ለተወሰኑ ጊዜያት ለእርባታው ስራ እንቅፋት ሆኖ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።
ይህንን ችግር ማዕከሉ ከአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 10 ፅዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበርና በሁለት ማህበራት በማደራጀት በኮምፖስት ስራ ለሃያ ሰዎች የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
በመሆኑም በአንድ በኩል የእርባታ ስራውን ለማቀላጠፍና የአካባቢውን ፅዳት ከመጠበቅ ባሻገር ማህበራቱን ከኮምፖስት ሽያጭ ገቢ ራሳቸውን በኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ተደርጓል። ከዚህም ባሻገር ከኮምፖስት ዝግጅቱ ጎን ለጎን አረንጓዴ ተክሎችን በማልማት የኮሚሽኑን ግብ ለማሳካት የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል። በዚህም በአንድ ድንጋይ ሁለት፣ ሦስት ወፍ መምታት መቻሉ ማሳያ ነው።
መረጃው፦ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments