ሀገራችን የያዘችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለማሳካት የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለአየር ንብረት ደህንነት የድርሻችንን እናበረክታለን።
ሀገራችን የያዘችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለማሳካት የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለአየር ንብረት ደህንነት የድርሻችንን እናበረክታለን።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች ክረምት የተከሉትን የፍራ ፍሬ ችግኝ አቢዮት ቅርስ ትምህርት ቤት በመገኘት የእንክብካቤ ሥራ ሰርተዋል።
አመራሮችና ባለሙያዎቹ የተከሉትን ችግኝ በቦታው ላይ ተገኝተው መንከባከባቸው ሀገራችን የያዘችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከማሳካት አንፃር አሻራን የማኖር ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል።
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ሀገራችን የያዘችውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለማሳካት የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለአየር ንብረት ደህንነት የድርሻችንን አሻራ ማኖር ነው ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments