ኢትዮጵያ ከተመፅዋችነት ተላቃ የአፍሪካ የስንዴ ምርት ቁንጮ ሆናለች- አሻርቅ ኒውስ
ኢትዮጵያ ከተመፅዋችነት ተላቃ የአፍሪካ የስንዴ ምርት ቁንጮ ሆናለች- አሻርቅ ኒውስ
(አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
ኢትዮጵያ ከተመፅዋችነት ተላቃ የአፍሪካ የስንዴ ምርት ቁንጮ ሆናለች ሲል አሻቅ ኒውስ ዘግቧል::
ኢትዮጵያ ባለፈው አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪኳ በስንዴ ምርት እራሷን መቻሏን የገለጸው ሚዲያው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቁጥር አንድ የስንዴ አምራች በመሆን ታሪክ መስራቷን ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት በተከተለው የግብርና ፖሊሲ ምክንያት የስንዴ ምርትን በእጥፍ በማሳደግ ሀገሪቱን ከተረጂነት ማላቀቁን አሻርቅ በሪፖርታዥ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ፤ ኢትዮጵያ የስንዴ ምርትን ለማደግ ሥስት ምክንያቶችን ማለትም ከፍተኛ የመስኖ እርሻ መስፋት፣ ምርጥ ዘር እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲሁም አዳዲስ የግብርና ፖሊሲ መከተል መሆኑን ገልጿል።
ኢትዮጵያ 112 ሚሊየን ሄክታር መሬት ያላት ሲሆን ከዚህም ውስጥ 38 ሚሊየን ሄክታር ለግብርና ምቹ መሆኑን ገልጿል።
ይህም በአመት በአንድ የግብርና ወቅት ብቻ 100 ሚሊየን ኩንታን ስንዴ ለማምረት እንደሚያስችል ገልጿል።
በ2023 የስንዴ ምርት ከ15 ሚሊየን ቶን ወደ 23 ሚሊየን ቶን በ2024 ማደጉን በዘገባው የተገለጸ ሲሆን ኢትዮጵያ የዓመት የስንዴ ፍጆታ 8 ሚሊየን ቶን ብቻ መሆኑን አሻርቅ ቢዝነስ በአረብኛ ቋንቋ ባወጣው ዘገባ ገልጿል።
መቀመጫውን ሳውዲ አረቢያ ያደረገውና ተደራሽነቱን ከአረቡ ዓለም አልፎ በመላው ዓለም ያደረገው አሻርቅ ኒውስ በዋናነት ትኩረቱን በኢኮኖሚ፣ በገንዘብና በዓለም አቀፍ የንግድ ዜናዎች ላይ አድርጎ የሚሠራ ሲሆን ከብሉምበርግ ጋር አጋርነት በመፍጠር ጭምር የሚሠራ ሚዲያ መሆኑ ይታወቃል።
#ከማምረትበላይ
#BeyondProduction
ምንጭ፡- ግብርና ሚንስቴር
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments