መንግስት  ከህዝብ ጋር ሆኖ እንጅ  ብቻውን ሌብ...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

መንግስት  ከህዝብ ጋር ሆኖ እንጅ  ብቻውን ሌብነትን ዜሮ አያደርስም።(ም/ኮ ሎኮ ዳለቻ)

መንግስት  ከህዝብ ጋር ሆኖ እንጅ  ብቻውን ሌብነትን ዜሮ አያደርስም።(ም/ኮ ሎኮ ዳለቻ)


ህዳር፤29/2010 ዓ.ም 


የአርሶ አደር ማቋቋም ዘርፍ  በልማት ምክንያት  ከይዞታቸው  ለተነሱ   አርሶ አደሮች  ከአራት ክፍለከተሞች ለተውጣጡ   25 ማህበራት 25 ሱቆች በእጣ  አከፋፈለ። 

ተነሺዎቹ  በይዞታ ማረጋገጥና  የጋራ መኖሪያቤት  ዙሪያ ከክፍለከተማ እስከ ወረዳ ድረስ  የገጠሟቸውን     የመልካም አስተዳደር  ችግሮች  በዝርዝር   ያነሱ ሲሆን  መንግስት ችግሩን ደረጃ  በደረጃ  ለመፍታት ጥረት ቢያደርግሞ  ህዝብ ከጎኑ ካልቆመ ብቻውን ሌብነትን ዜሮ አያደርስም  ከመንግስት ጎን ቁሙ  የሚል ምላሽ ም/ኮሚሽነሯ  ሰጥተዋል።   

ከልኬት አወሳሰድ ጋር ተያይዞ የራሱ መመሪያ እንዳለውና  አርሶ አደሩ  እየኖረበት ከሆነ ይለካለት ተበሎ  ለክፍለከተማና ወረዳ  አቅጣጫ እንደወረደ  ለተሳታፊዎቹ   ያብራሩት  የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረጋሳ ባይሳ ናቸው።

በመጨረሻም   ማህበራቱ  በተላለፈላቸው  ሱቅ መደሰታቸውን ገልፀዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments