ከተማ ግብርና ከኢኮኖሚ፣ከማህበራዊ እና ከስነ ምህዳር አንጻር ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
ከተማ ግብርና ከኢኮኖሚ፣ከማህበራዊ እና ከስነ ምህዳር አንጻር ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤3/4/2018 ዓ.ም
በከተማ ግብርና ዘርፍ በእፀዋት ሀብት ልማት እና እንሰሳት ሀብት ልማት ስራዎች ዙሪያ ለክፍለከተማ እና ወረዳ ባለሙያዎች የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የሌማት ትሩፋት እንደሀገር ትኩረት የተሰጠው በከተማ የሚኖረው ህብረተሰብ ራሱ አምርቶ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ታስቦ እንደሆነ እና ከሚሰራው የስራ ስፋትና እየተፈጠረ ካለው ለውጥ አንጻር ሲታይ ያለው የሰው ኃይልና ቴክኖሎጅው በቂ ስላልሆነ መስተካከል እንዳለበት ም/ኮ ሙሀመድ ልጋኔ አብራርተዋል።
አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ገቢ ለማሻሻል፣ነባር የከተማ አርሶአደሮች ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር ለቤተሰብ ፍጆታ የሚሆን የግብርና ምርት በማስገኘት የሥነ ምግብ ፍላጎት ለማሻሻል የከተማ ግብርና ወሳኝ እንደሆነ ተብሯርቷል፡፡
የስልጠናው አላማ በእጸዋትና እንስሳት ልማት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም ፣የታዩ የአደረጃጀት አመለካከት፣እውቀት ክህሎት፣የግብዓትና ቴክኖሎጅ አጠቃቀም እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ችግሮችን ለመለየት ታስቦ እንደሆነ በሰነዱ ላይ ተነስቷል፡፡
ከተማ ግብርና ከኢኮኖሚ፣ከማህበራዊ እና ከስነ ምህዳር አንጻር የከተማ ግብርና ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡(ተስፋዬ ኪዳነማርያም የሰብል ባለሙያ)፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎቹ ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት የእጸዋት ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ እና እንስሳት ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ደጀኔ ምላሽ ሰጥተውበታል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments