ግብርና ሚኒስቴር ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር የሚገመ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ግብርና ሚኒስቴር ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር የሚገመቱ ግብዓቶችን አከፋፈለ፡፡

ግብርና ሚኒስቴር ከ2 ቢሊዮን በላይ ብር የሚገመቱ ግብዓቶችን አከፋፈለ፡፡


አዲስ በባ፤ ታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም


ግብርና ሚኒስቴር ለምግብ ሥርዓት ማጠናከርያ ፕሮግራም የሚሆኑ 258 መኪናዎችን እና 1 ሺህ 830 የሞተር ብስክሌቶችን ዛሬ ለክልሎች አስረክቧል። 
‎ተሽከርካሪዎቹ በተለይም በገጠሩ አካባቢ ዝቅተኛ አቅም ያላቸው ወጣቶች፣ ሴቶች፣ አርሶ እና አርብቶ አደሮች የምግብ ሥርዓት እንዲሻሻል የሚሰሩ ባለሙያዎችን እና የላቦራቶሪ ቁሶችን ለማጓጓዝ እንደሚውሉ በርክክቡ ወቅት ተገልጿል።
‎ሚኒስቴሩ ከዚህ በተጨማሪ የአየር ንብረትን ለሚቋቋም የስንዴ እሴት ሰንሰለት ፕሮግራም 9 መኪኖች፣ 24 የሞተር ብስክሌቶች፣ የውኃ መሳቢያ ሞተር እንዲሁም 100 የመለዋወጫ ዕቃዎችን የያዙ ሳጥኖችን ለክልሎች አስረክቧል።
‎ይህም በኢትዮጵያ የተጀመረውን የበጋ መስኖ ልማትን ይበልጥ ለማስፋፋት እንደሚያግዙ ነው የተገለፀው።
‎የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት፤ ለሁለቱም ፕሮግራሞች ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው ድጋፍ ለክልሎች ተደርጓል።
‌‎ተሽከርካሪዎቹ ኢትዮጵያ የያዘችውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ለማሳካት አጋዥ መሆናቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ድጋፉ ከልማት አጋሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንደቀረበ ጠቁመዋል።‎
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽንም የዚህ መድረክ አካል ሆኗል፡፡

ምንጭ፡- EBC


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments