አምራች የሆነ የከተማ ነዋሪ  በመፍጠር  የምግብ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

አምራች የሆነ የከተማ ነዋሪ  በመፍጠር  የምግብ  ፍጆታውን  ማረጋገጥ ወሳኝ ነው(ም/ኮ መሀመድ ሊጋኒ)

አምራች የሆነ የከተማ ነዋሪ  በመፍጠር  የምግብ  ፍጆታውን  ማረጋገጥ ወሳኝ ነው(ም/ኮ መሀመድ ሊጋኒ)


አዲስ አበባ፤6/4/2018 ዓ.ም

የ90 ቀን የሌማት ትሩፋት፣የህዳር ወር  ሪፖርት እና በመደመር መንግስት እይታ የከተማ ግብርና ልማት የተሻሻለ  የምርት ማሳደግ ግቦች እቅድ ለግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ቀርቦ  ተገመገመ፡፡

በሁሉም ክፍለከተማ ሰፊ የሌማት  ትሩፋት ንቅናቄ መኖሩ፣ከጊዜ ወደ ጊዜ የሪፖርት ጥራት እየተሻሻለ መምጣቱ፣ ክፍለከተሞች  የግብአት አቅርቦት  ችግርን ለመፍታት በየፊናቸው ጥረት እያደረጉ መሆናቸው  እና የገበያ ማረጋጋት  ስራ በስፋት መሰራቱ በግምገማው ወቅት የታዩ  ጠንካራ ጎኖች  ሲሆኑ ስታንዳርድ ያልጠበቀ የላሞች ሸድ  መኖሩ ጥራት የሌለው  የመኖ ስርጭት መኖሩ በክፍተት የተነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡
 
የኑሮ ውድነትን ፣ሌብነትን፣ሰፈርተኝነትን፣ መንደርተኝነትን ፣ጎጠኝነትን እና ጠባቂነትን ለመቀነስና ተረጅነትን ዜሮ  ለማድረስና መሬትን ጦም ማሳደርን ለመከላከል  የከተማ ግብርና ልማት የተሻሻለ  የምርት ማሳደግ ግቦች እቅድ  አቅዶ ማንቀሳቀስ  አስፈላጊ እንደሆነ ም/ኮምሽነሩ  አያዘው ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments