የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የፀጥታ አካላት እገዛ የሚያስፈልጋቸው አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ ፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የፀጥታ አካላት እገዛ የሚያስፈልጋቸው አርሶ አደሮችን ሰብል ሰበሰቡ ፡፡
አዲስ አበባ፤ 06/2018 ዓ.ም
ክፍለ ከተማ አስተዳደሩ የፖሊስ አባላትን በማስተባበር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ዳንሴ በሚባል አካባቢ እገዛ የሚያስፈልጋቸው አርሶ አደሮችን የደረሰ የስንዴ ሰብል የመሰብሰብ ስራ ሰርቷል።
በመርሀ ግብሩ የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና፣ የክፍለ ከተማው የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት መካሻ፣ የየካ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ እና ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሀይሉ አስካለ እንዲሁም የወረዳው አመራሮችና የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና እንደገለፁት የአርሶ አደሩ ሰብል በዝናብ እንዳይበላሽ በወቅቱ እንዲሰበሰብ የፀጥታ አካላቱ ያደረጉት መልካም ተግባርን በማመስገን እንደ ሀገር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አቅጣጫ መሰረት ወደ ስራ የተገባው የ2 አሀዝ እድገት እቅድን ለማሳካት እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያሳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ መሰረት መካሻ በበኩላቸው በ2017/18 የምርት ዘመን እንደ ክፍለ ከተማ የማስፋፊያ አካባቢ ለሚገኙ የወረዳ 3፣ 10፣ 11 እና ወረዳ 12 በዘር የተሸፈነው መሬት 708 ሄ/ር ሲሆን ወደ 768 አርሶ አደሮች 1,416 ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ መጠቀም መቻላቸውን እና ከዚህ ውስጥ 47 የሚሆኑት አርሶ አደሮች የስንዴ ምርጥ ዘር ከኦሮሚያ ክልል አሰላ በማስመጣት በመስመር እዲዘሩ መደረጉን እና ከዚህ መሬት ውስጥ 2,644 ኩ/ል ምርት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የፀጥታ አካላቱ ህገ ወጥ ተግባራትን ከመከላከል ጎን ለጎን በችግር ጊዜ ለህብረተሰቡ ደራሽነቱን ያሳየበት መሆኑን የየካ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ ገልፀዋል ።
ከፍተኛ አመራሩ ከፖሊስ መምሪያና ከየፖሊስ ጣቢያ የተውጣጡ 174 የፖሊስ አባላትን በማሳተፍ እና የክፍለ ከተማና የወረዳ 10 አመራሮችና ባለሙያዎች ፣ የአርሶ አደር ኮሚቴዎችን በማስተባበር ሰብሉን በማጨድ፣ በመሰብሰብና በመከመር የደረሰውን ሰብል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ ማድረግ ተችሏል።
አርሶ አደሮቹ በተደረገላቸው እገዛ እጅግ መደሰታቸውን ገልፀው ያገዟቸውን፣ ያስተባበሩትን እና ከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል።
ምንጭ ፡- የየካ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments