በመረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ስርዓት ተገቢ የሆነ መግባባት በመፍጠር ወሳኝነት አለው፡፡
በመረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ስርዓት ተገቢ የሆነ መግባባት በመፍጠር ወሳኝነት አለው፡፡
አዲስ አበባ፤7/4/2018 ዓ.ም
በከተማ ግብርና ዘርፍ በእፀዋት ሀብት ልማት እና እንሰሳት ሀብት ልማት ስራዎች ዙሪያ ለክፍለከተማ እና ወረዳ ባለሙያዎች የተዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።
የስልጠናው አላማ በእጸዋትና እንስሳት ልማት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም ፣የታዩ የአደረጃጀት አመለካከት፣እውቀት ክህሎት፣የግብዓትና ቴክኖሎጅ አጠቃቀም እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ችግሮችን ለመለየት ታስቦ እንደሆነ የሰብል ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋየ ኪዳነማርያም ገልጸዋል፡፡
በመረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ስርዓት ተገቢ የሆነ መግባባት ለመፍጠር ፣ከግብአት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የመጠንም ሆነ የጥራት ችግሮችን ለመፍታት እና በእንስሳት ሃብት ልማት ተጠቃሚዎች የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ንቅናቄው አስፈላጊ ሆኖ ተገንቷል ፡፡( ዘላለም ታምራት የእንስሳት ዕርባታና ተዋዖ ቡድን መሪ)
ከምርምር ማእከላት የተገኙ እና ከውጭ ሀገር የሚመጡ የእንስሳት ምርት ማሻሻያ ቴክኖሎጅዎችን አሟልቶ ከሀገራችን ከተሞችና ከተሞች ዙሪያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማካተት መጠቀም የሚያስችል ድጋፍ በመስጠት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል የእንስሳት ዕርባታ ፓኬጅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ቡድን መሪው አያይዘው ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ከታሳቲፊዎቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት የእጸዋት ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ እንሰኔ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበት ስልጠናው ተጠናቋል ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments