መልካም ተሞክሮዎች በመጋራት የቀጣናውን ብሎም የ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

መልካም ተሞክሮዎች በመጋራት የቀጣናውን ብሎም የአህጉሪቱን ዜጎች ተጠቃሚነት ማሳደግ ይጠበቅብናል፡፡ (የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ፓርላማ ትብብር ልዑካን ቡድን)

መልካም ተሞክሮዎች በመጋራት የቀጣናውን ብሎም የአህጉሪቱን ዜጎች ተጠቃሚነት ማሳደግ ይጠበቅብናል፡፡ (የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ፓርላማ ትብብር ልዑካን ቡድን)


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም


የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ፓርላማ ትብብር ልዑካን ቡድን አባላት በምሥራቅ አፍሪካ ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ያለንን የተፈጥሮ ሀብትና መልካም ተሞክሮዎች በመጋራት የዜጎችን ሕይወት ማሻሻል ይገባናል ሲሉ በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በነበራቸው ጉብኝት ላይ ገልፀዋል፡፡ 

ከ11 ሀገራት የተውጣጣው የልዑካን ቡድን አባላት የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 በመገኘት ሞዴል የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን የተቀናጀ የከተማ ግብርና ሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ የምስራቅ አፍሪካ ብሎም የአህጉሪቱን የሥነ-ምግብ እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ልምድና ተሞክሮዎችን ማስፋትና ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሆነ ያነጋገርናቸው የልዑካን ቡድኑ አባላት ተናግረዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአርሶ አደሮችና ለከተማው ነዋሪ ልዩ ትኩረት በመስጠት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል በስፋት እየሰራች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ ከአቋቋማቸው አስፈፃሚ አካላት መካከል አንዱ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ሲሆን አርሶ አደሮችን ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ፣ የከተማ ግብርና እንዲስፋፋና እንዲዘምን ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑን እና ዛሬ ልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ የተመለከታቸው ለዚህ ማሳያ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑም በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልና በግለሰቦች ፋርም ተገኝተው በተመለከቱት ነገር እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments