ደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ ምርትና ምርታ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ ምርትና ምርታማነትን እናረጋግጥ!!

ደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ ምርትና ምርታማነትን እናረጋግጥ!!


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም


የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሹ አርሶ አደሩ ምርቱን ቶሎ መሰብሰብ አለበት። በአብዛኛው የመኸር ሰብል በተዘራባቸው አካባቢዎች የደመና እና የዝናቡ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሹ በተደራጀ መንገድ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም፣በልማት ቡድን፣በአደረጃጀቶች በደቦ እና ሌሎች የማህበረሰብ አደረጃጀቶችን ተጠቅሞ ሰብሎቹን ከብክነት እንዲታደግ መሰብሰብ አለበት ።የተሰበሰቡ ሰብሎችም ዝናብና እርጥበት በማያስገባ መልኩ እንዲከመሩ በማድረግ የምርት ብክነትን መከላከል ይገባል።ወቅቱን ያልጠበቀው ይህ ዝናብም ለሰብል ተባዮች መራቢያ አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር ስለሚችል አርሶ አደሩ ወቅቱን የጠበቀ አሰሳ ማድረግም ይኖርበታል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments