መልካም ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት ለበለጠ ውጤታማነት ያተጋል፡፡
መልካም ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት ለበለጠ ውጤታማነት ያተጋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አስተዳደር ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በመገኘት በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና ሪፎርም ሥራዎች፣ ዕቅድን የሥራ መመሪያ አድርጎ ስለመስራትና በበጀት አጠቃቀም፣ በግዥ ሂደትና ጠቅላላ አገልግሎት፣ በፋይናንስና የሰው ሃብት አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የልምድ ልውውጥ አድርገናል፡፡
በተጨማሪም በኢዲት ትግበራ፣ በICT አስተዳደር፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መከላከልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ስለመፍታት፣ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር እና አጠቃላይ የአስተዳደር ዘርፍ እንቅስቃሴ ላይ ልምድ መውሰድ ተችሏል፡፡
የትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎችም መልካም አቀባበል አድርገው ያላቸውን ልምድና መልካም ተሞክሮ በዝርዝር በቃል፣ በሰነድና በአካል ምልከታ አካፍለውናል፡፡
በቃል ውይይት፣ በሰነድ ማስረጃ እና በአካል ምልከታ በልምድ ልውውጥ ሂደቱ በርካታ ትምህርቶች መውሰድ ተችሏል፡፡
በልምድ ልውውጡ ላይ የተሳተፉት የኮሚሽኑ ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ከወሰዱት ልምድ ሰፊ ትምህርት መቅሰማቸውን እና ወደ ኮሚሽኑ ወስደው እንደሚያሰፉት ገልፀዋል።
አያይዘውም የትምህርት ቢሮ አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ባለሙያዎችም ከአቀባበል ጀምሮ ያላቸውን ልምድና መልካም ተሞክሮ በግልጽ እና አስተማሪ በሆነ መልኩ ስላካፈሉን ከፍተኛ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments