የግብርና ሥራ የየዕለት ድጋፍና ክትትል ይፈልጋል...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የግብርና ሥራ የየዕለት ድጋፍና ክትትል ይፈልጋል፡፡

የግብርና ሥራ የየዕለት ድጋፍና ክትትል ይፈልጋል፡፡

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

በልደታ ክፍለ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የከተማ ግብርና ስራዎችን (ነባር ማስቀጠል፣ አዲስ ማደራጀት፣ በተቋማት፤ በፋሚሊ ቢዝነስና በማህበራት የተሰሩ ስራዎች) ጉብኝት ተካሄደ።

የልደታ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ እንደገለፀልን በልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እና በምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አራርሳ ድሪባ የተመራ ቡድን በክ/ከተማው እየተከናወኑ ያሉ የከተማ ግብርና ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ ከሰው ተኮር ተግባራቶቻችን አንዱ የሆነውን የከተማ ግብርና ስራ በጥራትና በስፋት በመስራታችን በህብረተሰቡ ዘንድ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አምጥተናል ሲሉ መናገራቸውን አቶ ፍቃዱ የላኩልን መረጃ ይጠቁማል፡፡

ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አራርሳ ድሪባ በበኩላቸው የጉብኝቱ ዓላማ የከተማ ግብርና ተግባር ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ እገዛ ለማድረግ መሆኑን የገለፁ መሆኑን የጽ/ቤት ኃላፊው ገልፀውልናል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments