ግብና ከማምረትም በላይ ነው!።

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ግብና ከማምረትም በላይ ነው!።

ከሸማችነት ወደ አምራችነት!
ግብና ከማምረትም በላይ ነው!።


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም


አርሶአደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመሆን በከተማ ግብርና የተሰሩ የከተማ ግብርና ልማት እና የሌማት ትሩፋት ሥራዎች በመስክ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና አቶ ባዮ ሽጉጤ፣ ም/ኮሚሽነሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የዘርፉ የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ፣ የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች በጉብኝቱ ተሳታፊ ሆነዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በከተማ ግብርና ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም የከተማዋ ነዋሪ ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገር እየተሰራ ባለው ሥራ በአሁኑ ጊዜ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚ መኖሩን ተናግረዋል።

ተጠቃሚዎች አመራሮችና ባለሙያዎች ስለጎበኟቸውና ለሚደረግላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments