ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የሌማት ትሩፋት አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡
ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት የሌማት ትሩፋት አስተዋጽኦ የጎላ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አመራሮች ዋና አቶ ባዮ ሽጉጤ፣ ም/ኮሚሽነሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የዘርፉ የክ/ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የቦሌ፣ የአቃቂ እና የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች በከተማ ግብርና ዘርፍ እየተፈጠረ ያለውን የሥራ ዕድል፣ የአርሶ አደሮች ልማት እና በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ተዘዋዉረው ጎብኝተዋል።
በመስክ ምልከታው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ በከተማ ግብርና ዘርፍ እየተሰራ ያለው ሥራ የከተማችንን ነዋሪ የኑሮ ውድነት ለማቅለል እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ያስችላል ብለዋል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ በቦሌ፣ በአቃቂ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች የተመረጡ ቦታዎችን እና የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከልን የእንስሳት ሃብት ልማት፣ የተቀናጀ ከተማ ግብርና፣ የእንቁላል ዶሮ ክላስተር፣ የንብ ክላስተር፣ የዶሮ እርባታ እንዲሁም የጓሮ አትክልት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በመስክ ምልከታው ላይ የከተማ ግብርና ልማት የስራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ፣ የምርት አቅርቦትና የገበያ ትስስር እንዲሁም የተገኙ ውጤቶች ምልከታ እና በሚመለከታቸው አካላት ገለፃ ተደርጓል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments