አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው መልማ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው መልማት እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

አርሶ አደሮች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው መልማት እንዲችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

 

አዲስ አበባ፤ታህሳስ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

 

በልማት ምክንያት ከይዞታቸዉ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ከደረሰባቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት በማላቀቅ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ በከተማ አስተዳደሩ እና በኮሚሽኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡

 

አሰራሮችን በመዘርጋት የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ምዝገባ እና ልየታ በማካሄድ፣ ያሉበትን የኢኮኖሚ ደረጃ ታሳቢ በማድረግ በዘላቂ ቀጥታ ድጋፍ፤ በስራ እድል ፈጠራ፤ የጋራ መኖሪያ ቤት እና የመስሪያ ቦታ በፍትሃዊነት፣ በግልጽኝነት እና በትክክለኛ ህጋዊ አሰራር እና የአርሶ አደሮችን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ በርካቶችም ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

 

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አስተዳደር የልማት ተነሺ አርሶ አደር ናችሁ ተብለው የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተወሰደው መረጃ ላይ ችግር አለበት በሚል የቀረበውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ የማጥራት ሥራ ሲሰራ የቆየ መሆኑ ተገልጷል፡፡

 

በዛሬው ዕለትም በማጥራት ሂደቱ የተገኘውን ግኝት መነሻ በማድረግ ያጋጠመውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ፣ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ እና ሌሎች አመራሮች ቅሬታ አቅራቢዎቹን አወያይተው የተገኘውን ግኝት የጋራ አድርገዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments