ህገወጥ  እርድ  በዋናነት  የሚከናወነው በምሽት...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ህገወጥ  እርድ  በዋናነት  የሚከናወነው በምሽት ጨለማን ተገን በማድረግ  ይከናወናል፡፡

ህገወጥ  እርድ  በዋናነት  የሚከናወነው በምሽት ጨለማን ተገን በማድረግ  ይከናወናል፡፡

 

 

አዲስ አበባ፤22/4/2018  ዓ.ም

 

 

በህጋዊ ቄራዎች  የሚከናወነው  የእርድ  አገልግሎት ህጋዊ  ሲሆን ለግል ፍጆታ ሲባል በየቤቱ የሚከናወን ኢ-መደበኛ እርድ ክንውን  ህገወጥ ነው ብሎ መውሰድ ባይቻልም ነገር ግን  በህጋዊ  ቄራዎች  ቢታረዱ  የሚመከር  ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከነዚህ ውጪ የሚከናወኑ ማንኛውም  የእርድ ክንውን  ዓይነቶች በህገወጥ  እርድ  የሚታዩና  ተቀባይነት  የሌላቸው  እንደሆኑ ይነገራል፡፡

 

 

የህገወጥ እርድ ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ፣ በህግ የሚያስጠይቅ በመሆኑ፣ ትክክለኛ የሆነ የገቢ መረጃን ለመደበቅ፣ ከግብር ለመሸሽ እና በአቋራጭ ለመበልጸግ በመሆኑ የእርድ ስራው የሚከናወነው ሌሎች ሰዎች ሊያዩት በማይችሉበት ቦታና ሰዓት ነው፡፡ ለዚህም ከሚጠቀሱ ቦታዎች መካከል፡-በየስርቻውና ሸለቆዎች ፣በወንዞች ዳርቻ  በቆሻሸ ገንዳዎች ውስጥ፣ በእንስሳት ገበያዎችና ማሳደሪያዎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡

 

ህገወጥ  እርድ  በዋናነት  የሚከናወነው፡-በምሽት ጨለማን ተገን በማድረግ  በበዓላት ሰዓት ከፍተኛ የእርድ መጠን የሚበዛ በመሆኑ  ተቆጣጣሪ  አካላት ትኩረት በሚቀንስበት ሰዓት በተለይ  ሌሊት እና ንጋት ላይ የህገወጥ እርድ የሚከናወንበት ሰዓት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments