"ካይዘን የማህበራትን የስራ ባህል ያሻሽላል"

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

"ካይዘን የማህበራትን የስራ ባህል ያሻሽላል"

"ካይዘን የማህበራትን የስራ ባህል ያሻሽላል"
በማዕሰሉ ለማህበራት የካይዘን ሥልጠና እየተሰጠ ነው።


አዲስ አበባ (ታኅሣሥ 24/2018 ዓ.ም)



በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል በሶስቱ ክላስተሮች ማለትም በወተት ከብት እርባታ፣ በዳልጋ ከብት ማድለብ እና በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ ማህበራት በካይዘን ዙሪያ ሥልጠና ተሰጥቷል።
ሥልጠናው የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር በሁለት ክፍሎች የተሰጠ ሲሆን በመጀመሪያው ክፍል የካይዘን ፍልስፍና፣ ምንነትና አስፈላጊነት በአቶ ማረፊያ ታዬ፤ እንዲሁም በሁለተኛው ክፍል ብክነትን መለየትና ማስወገድ እንዲሁም የእሴት ሠንሠለት ምንነት በሚል ርዕስ በአቶ አለማየሁ አጋዥ ቀርቧል።
ካይዘን የሥራ ባህልን ከማሻሻልና የአመለካከት ለውጥን ከመፍጠር ባሻገር ተቋማትንና ማህበራትን ወደ ማያቋርጥ የለውጥ ጎዳና ለማሸጋገር ወሳኝ መሆኑ በሥልጠናው ተጠቁሟል። 
በማዕከሉ የገበያ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሣራ ንጉሴ የተሰጡት ሥልጠናዎች የማህበራት የማምረት አቅምና ውጤታማነት ላይ ከፍተኛ እሴት የሚጨምሩ መሆናቸውን ገልፀው ሁሉም ማህበራት ካይዘንን በአግባቡ መተግበርና መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
መረጃው የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments