መጭውን የገናና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

መጭውን የገናና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ የግብርና ምርት በበቂ ሁኔታ እየቀረበ ይገኛል፡፡

መጭውን የገናና የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ የግብርና ምርት በበቂ ሁኔታ እየቀረበ ይገኛል፡፡


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 24 ቀን 2018 ዓ.ም



ለመጪው የገናና የጥምቀት በዓል የሚውሉ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ሁሉም ክፍለ ከተማ ላይ ያሉ የከተማ ግብርና ቤተሰብ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡

በተለይም በክርስቲያኖች ዘንድ በዓሉ ከ40 ቀን በላይ ተፆሞ ከሃይማኖታዊ ስርዓቱ ባሻገር የተለያዩ ባህላዊ ምግቦችን በማዘጋጀትና በጋራ ማዕድ በመቋደስ የሚከበር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዝግጅቱ ሰፊ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና የምርት እጥረት እንዳያጋጥም የከተማ የከተማ ግብርና ምርት ከአምራቹ በቀጥታ ለሸማቹ እንዲደርስ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በዚህም ለገና በዓል ከክፍለ ከተሞች የግብርና ምርት በተጨማሪ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ብቻ ከ500 ሺ በላይ እንቁላል፣ የወተት እና የወተት ተዋጽኦ ፤ የደለቡ በሬዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments