በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ ቄራዎች...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ ቄራዎች ህብረት ምስረታ አከናውነዋል!፡፡

በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ ቄራዎች ህብረት ምስረታ አከናውነዋል!፡፡


አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2018 ዓ.ም


የምስረታው ዋና ዓላማ በአዲስ አበባ እና በሸገር ከተማ የሚገኙ ቄራዎች ህገወጥ የእንስሳት እርድን በጋራ ለመከላከልና ሌሎች ስራዎች በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል ።
በምስረታው  የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የሸገር ከተማ ም/ክ  ስራአስኪያጅ አቶ ጫላ ለሚ እና የአዲስ አበባ ከተማ  የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሰልጣን ም/ክ  ስራ አስፈፃሚ አቶ  ፍቅሬ ግዛው  እንዲሁም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝና የዘጠኙም ቄራዎች አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
ከዚህ ቀደም በሸገር እና በአዲስ አበባ ከተማ ቄራዎች መካከል የነበረውን መገፋፋት በማስቀረት በመተባበር ስራዎችን በቅንጅት በመስራት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ትርፋማነታችንና ውጤታማነታችንን ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ተናግረዋል ።
በጋራ መስራት ባለመቻላችን ብዙ ችግሮችን ተጋፍጠናል አሁን ይህን የጋራ  ስምምነት መፈራረማችን ችግሩን በመቅረፍ  ህገ ወጥነትን ከመከላከል በተጨማሪ ስጋን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ መንገድ ያመቻቻል ሲሉ  የተወካዮች ምክር ቤት አባልና የሸገር ከተማ ም/ክ  ስራአስኪያጅ አቶ ጫላ ለሚ ገልጸዋል 
ሁለቱ ከተሞች ከተፈጥሯዊ አቀማመጣቸው ጀምሮ በብዙ ነገር የተሳሰሩ በመሆናቸውና ጤንነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት እርድ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የጋራ ዓላማቸውም በመሆኑ ይህ ስምምነት ስራውን ያቀለዋል በማለት ይህን ሀሳብና መድረክ ላዘጋጁ አመራሮችና አካላት ምስጋና ይገባችኋል በማለት  የአዲስ አበባ ከተማ  የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለሰልጣን ምክ  ስራ አስፈፃሚ አቶ  ፍቅሬ ግዛው ተናግረዋል ።
ህገወጥ የእንስሳት እርድን የሚመለከት ሰነድ 
በአዲስ አበባ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሰርተፊኬሽን ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  በሆኑት ዶ/ር አስናቀ አወቀ የቀረበ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱት በርከት ያሉ ሀሳብና አስተያየቶች አመራሮቹ ምላሽ ሰጥተዋል ።
በመጨረሻም የዘጠኙም ቄራዎች አመራሮች የስምምነት ሰነድ በመፈራረም  "ህብረታችንን በመደመር እናጸናለን" በሚል ቃል ኬክ በመቁረስ ስነስርዓት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments