የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ልዑካን ቡድን አባላት ማዕከሉን ጎበኙ።

የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ልዑካን ቡድን አባላት ማዕከሉን ጎበኙ።


 አዲስ አበባ (ታኅሣሥ 25/2018 ዓ.ም)


የንግድ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ልዑካን ቡድን አባላት የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከልን ጎበኙ።

የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ስለማዕከሉ አጠቃላይ ሁኔታ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በማዕከሉ በሶስት ክላስተር በተለይም በእንቁላል ጣይ የዶሮ እርባታ፣ በዳልጋ ከብት ማድለብ እና በወተት ከብት እርባታ ምርቶቹን ከማዕከሉ ሱቆች  በተጨማሪ በመሃል ከተማ ባሉ ሱቆች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ስራ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የአርሶ አደር መልሶ ማቋቋም ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ማዕከሉ በዋናነት የተቋቋመው የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም ሲሆን የገበያ ማረጋጋት ስራው ላይም ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሁሉም ክላስተሮች እየተከናወኑ ያሉ የእርባታ ስራዎችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ በጉብኝቱ ደስተኛ መሆናቸውንና እንደዚህ ዓይነት ሰው ተኮር ተግባራት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መስፋፋት እንደሚኖርባቸው ሃሳባቸውን
መረጃው የእንስሳት ልህቀት ማዕከል ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments