በታታሪ አርሶ አደሮች ህብረት ትውልድ እየተቀረፀ ነው።
በታታሪ አርሶ አደሮች ህብረት ትውልድ እየተቀረፀ ነው።
አዲስ አበባ፣25/4/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙት የካ፣ ቦሌ እና ለሚኩራ ክፍለከተሞች በትምህርቱ ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት የምስረታ ጉባኤ አካሄዱ።
በ2010 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቀድሞ ከንቲቫ በነበሩት ክቡር ድሪባ ኩማ እና የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በነበሩት ለማ መገርሳ (ዶ/ር) የመሰረት ድንጋይ ተጥሎ በ2014 ዓ.ም ዪኒፋርም አካዳሚ በሚል ስያሜ ለልማት ተሽ አርሶ አደሮች ገቢ ማስገኛ ይሆን ዘንድ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደተጀመረ በምስረታ ጉባኤው ላይ ተነስቷል።
ም/ኮ ሎኮ ዳለቻ በብዙ ውጣ ውረድ አልፋቹህ ለዚህ ውጤት በመብቃታቹህ የብዙ ልማት ተነሽ አርሶ አደሮቻችን ምሳሌዎች በመሆናቹህ ደስ ሊላቹህ ይገባል እኛም በእናንተ ኮርተናል ብለዋል።
በታታሪ ገበሬዎች ህብረት የተመሰረተው ዪኒ ፋርም አካዳሚ በእድሜ ተንሹ በተግባሩ ግን ትልቅ መሆኑን በተለያዩ ማሳያዎች ገልፀው በ3ቱም ክፍለከተሞች ቅርንጫፎቻቸውን አስፍተው እንደሚቀጥሉ አብራርተዋል።
የኮሚሽኑ አርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሳ ባይሳ፣የክፍለከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የህብረት ስራ ማህበር ማደራጃ ኮሚሽን አመራሮች፣ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች እና አባላቱ በተገኙበ አንድ ስያሜ እና አንድ ሰርተፍኬት እንዲኖር የምስርታ ጉባኤው በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ተካሂዷል።
ሌሊትም ቀንም በመስራት ባመጣችሁት ውጤት ከእናንተ አልፎ የኮሚሽኑን ስም በማስጠራታቹህ ምስጋና ይገባቹሀል። (የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረጋሳ ባይሳ)
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments