ማህበረሰቡ ጥራቱ፣ ጤንነቱ እና ኃይጅኑ የተጠበቀ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ማህበረሰቡ ጥራቱ፣ ጤንነቱ እና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት መጠቀም አለበት፡፡

ማህበረሰቡ ጥራቱ፣ ጤንነቱ እና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት መጠቀም አለበት፡፡


አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 25/04/2018 ዓ.ም አ/አ/ከ/ል/ኮሚሽን  



መጭውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ቄራ ድርጅት፣ ከሊኳንዳ ነጋዴዎች ማህበር እና ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡


የኮሚሽኑ የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የከተማችን ነዋሪዎች ኮሚሽኑ ቄራ ላይ በመደባቸው የሥጋ ምርመራ ሃኪሞችና የላብራቶሪ ባለሙያዎች የተመረመረ ጥራቱ፣ ጤንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ ሥጋ መጠቀም አለባቸው ብለዋል፡፡ 


አያይዘውም እንስሳው ሲገዛ በቁሙ በሚገባ ማየት፣ በእርድ ወቅትም ተገቢውን ጥንቃቄ መውሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሕገ-ወጥ የእንስሳት እርድ በወንዞች አካባቢ፣ በሆቴሎች ጀርባና ንጽህናቸውን ባልተጠበቁ አካባቢዎች ስለሚከናወን ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች ያጋልጣል ብለዋል፡፡


የአዲስ አበባ ቄራ ድርጅት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታክልቲ ገ/ሚካኤል ድርጅታቸው ለበዓሉ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
አክለውም ለመጪው የገና በዓል ከ4,000 በላይ በሬዎች እንዲሁም በግና ፍየሎች ለእርድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል፡፡


የአዲስ አበባ ልኳንዳ ቤት ማህበርም መጭውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጷል፡፡


የደንብ ባለስልጣን በበኩሉ ከህገወጥ እርድ፣ እንስሳት እና ሥጋ ዝውውር ጋር በተያያዘ በሁሉም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች ላይ ባሉ የደንብ ኦፊሰሮች አማካኝነት ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጷል፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቄራ የሥጋ ምርመራ ቡድን መሪ ዶ/ር ኦዳ በበኩላቸው ለመጭው የገና በዓል በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡


ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ኮሚሽኑ ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድ እና ሥጋ ዝውውርን መቆጣጠር በአዋጅ የተሰጠው ተግባር በመሆኑ በቄራዎች ላይ የሥጋ ምርመራ ዶክተሮችና የላብራቶሪ ባለሙያዎች በበቂ መጠን መድቦ 24 ሰዓት እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፡፡ 

ሌላው ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ህብረተሰቡ ንጽህናው የተጠበቀ የማረጃ ቁሳቁሶችን መጠቀም አለበት፤ ተረፈ ምርቶችንም በአግባቡ እንዲወገዱ መወገድ የሌለባቸው ደግሞ መዋል ላለባቸው አገልግሎት እንዲውሉ በተለይም ቆዳና ሌጦ በአግባቡ ለፋብሪካዎች እንዲገባ ማድረግ ይጠበቅበታል፤ ህገወጥ እርድና ሥጋ ዝውውርን በተመለከተም ከኮሚሽኑ ጋር አብሮ መስራት ይገባዋል ሲሉ ጥሪ አድርገዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments