"ማዕከሉ ከልምድ ልውውጥ ባሻገር የህፃናት የህልም እና ዝንባሌ መቅረጫም ጭምር እየሆነ ነው።"
"ማዕከሉ ከልምድ ልውውጥ ባሻገር የህፃናት የህልም እና ዝንባሌ መቅረጫም ጭምር እየሆነ ነው።" አቶ አሌክስ ደመቀ (የማዕከሉ ኃላፊ)
አዲስ አበባ፤ ታኅሣሥ 27/2018 ዓ.ም
ማዕከሉ ከልምድ ልውውጥ ባሻገር የህፃናት የህልም እና ዝንባሌ መቅረጫም ጭምር እየሆነ መሆኑን የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ ገለፁ።
ኃላፊው አክለውም ማዕከሉ በዋናነት የተቋቋመበት ዓላማ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም እና የምርቶች የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ቢሆንም ለተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትና በዘርፉ ለመሠማራት ለሚሹ ግለሰቦች የልምድ ልውውጥ ማዕከል መሆኑን አንስተዋል።
በየጊዜው ከሚደረጉ የሰው ተኮር ተግባራት ጉብኝቶች ባሻገር ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመጡ ህፃናትም በማዕከሉ በመገኘት ህልማቸውንና ዝንባሌያቸውን ለመቅረፅ እንዲችሉ በር እየከፈተ ይገኛል። በዚህም ለወደፊት የከተማ ግብርናን በትኩረት ሊሰራ የሚችል ተተኪ ትውልድ ለማፍራት የሚኖረው ድርሻ ቀላል የማይባል መሆኑን ተማሪዎችን ያስጎበኙት ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል።
መረጃው የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments