የሦስት ወራት የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የግብዓት...

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

የሦስት ወራት የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የግብዓት ስርጭት ተካሄደ።

 

አዲስ አበባ፤ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ3 ወራት የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ የግብዓት ስርጭት ፕሮግራም አካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይም 11,000 ዶሮዎችን፣ ለ3 ወር የሚሆን መኖ እንዲሁም ኬጂ ለ2,300 አቅመ ደካማ እና ልጆች ብቻቸውን ለሚያሳድጉ እናቶች ስርጭት ማድረግ ተችሏል።
 
የእለቱ የክብር እንግዳ በመሆን ፕሮግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አንፃር በርካታ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

አክለውም ኮሚሽኑ አምራችና ሸማችን በቀጥታ በማገናኘት ረገድ ከፍተኛ ውጤታማ ስራዎችን እየሠራ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ምግቤን ከጓሮዬ በሚል ሀሳብ የምንሠራቸው የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ ስራዎች ገበያውን እና የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አንፃር የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ህብረተሰቡ አውቆ ተግባሩን በላቀ ትጋት መስራት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments