የንብና የዶሮ ክላስተር መጀመሩ ከተማ ላይ አይቻ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የንብና የዶሮ ክላስተር መጀመሩ ከተማ ላይ አይቻልም የተባለውን አመለካከት  ሰብሯል፡፡

የንብና የዶሮ ክላስተር መጀመሩ ከተማ ላይ አይቻልም የተባለውን አመለካከት  ሰብሯል፡፡


አዲስ አበባ፣28/4/2018 ዓ.ም


በከተማ ደረጃ የወረደው የሱፐርቪዥን ቡድን  ባደረገው ድጋፍና ክትትል ግብረ-መልስ ላይ ከተቋሙ አመራሮች ጋር የጋራ ውይይት አድርጓል፡፡

አርሶ አደሩን  ከማቋቋም  አንፃር፣ ከተማ ግብርናን ከማስፋፋትና ከማዘመን አኳያ፣ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል እንቅስቃሴ እንዲሁም የሬጉላቶሪ ሥራዎ እጅግ በጣም ጥሩ መሆናቸውን ቡድኑ ገልጿል።

የንብና የዶሮ ክላስተር መጀመሩ ከተማ ላይ አይቻልም የተባለውን አመለካከት  ሰብሮ ጥሩ የስራ ባህል እንዲፈጠር አድርጓል በማለትም ከምልከታቸው ያገኙትን አንስተዋል።

ኮሚሽኑ የሚሰራውን ሥራ ብዙ ያልተረዱት አካላት አሉ፤ መሬት ላይ ወርዶ ለተመለከተው ግን እጅግ በጣም በርካታ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ይሰራል ብለዋል።

በማህበር  ተደራጅተው ሱቅ  የወሰዱ አርሶ አደሮች ፈጥነው  ወደ ስራ  መግባት እንዲችሉ  ሁኔታዎች ቢመቻቹና  የንግድ   አካባቢዎች የአካባቢን ገጽታ  ከመቀየር አንጻር ትልቁን ሚና  እንደሚጫወቱ  አንስተዋል፡፡

ከአርሶ አደር መብት ፈጠራ ጋር በተያያዘ ኮሚሽኑ ራሱ ጀምሮ ራሱ ስለማይጨርስ በተለይም መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ጋር ሰፊ ሥራ ይጠበቃል ብለዋል የቡድኑ አባላት።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ  አርሶ አደሩን ወደተሻለ የኑሮ  ደረጃ ለማሸጋገር   በጥንካሬ  እየተሰራ እንደሆነ አንስተው ያሉብንን  ክፍተቶች አሻሽለን  የነበሩንን   ጠንካራ  ጎኖች  እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡

አያይዘውም የሱፐርቪዥን ቡድኑ በግብረ-መልሱ በትኩረት ማየት ያለበትን ጉዳዮች በዝርዝር ጠቅሰዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments