ግብርናችን መሰረታዊ ፍላጎታችን ነው።

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ግብርናችን መሰረታዊ ፍላጎታችን ነው።

ግብርናችን መሰረታዊ ፍላጎታችን ነው።

አዲስ አበባ፤ ጥር 02 ቀን 2018 ዓ.ም

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ከማዕከል አመራሮች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች፣ ከክፍለ ከተማና ከወረዳ የዘርፉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ከክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ግምገማ እያደረገ ይገኛል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በሌማት ትሩፋት እና በንቅናቄ የተሰሩ ሥራዎች፣ በመደበኛው ሥራዎቻችን፣ በቁልፍ ተግባራት፣ በመደመር መንግስት የተሰጡ አቅጣጫዎች ላይ የተሰሩ ሥራዎችን በዝርዝር ማየት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ሌላው ዋና ኮሚሽነሩ በመግቢያ ንግግራቸው ያነሱት ጥንካሬዎችን፣ ክፍተቶችን፣ ምቹ ሁኔታዎችን እና ፈታኝ ጉዳዮችን በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ ውጤታማ የምንሆንበት አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments