ዕቅድና ሪፖርት ተናባቢ ሆኖ መሬት ላይ ሕይወት ሊኖረው ይገባል። ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ
ዕቅድና ሪፖርት ተናባቢ ሆኖ መሬት ላይ ሕይወት ሊኖረው ይገባል። ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ
አዲስ አበባ፤ ጥር 02 ቀን 2018 ዓ.ም
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ አርሶ አደሮችን መልሶ ማቋቋምና ማልማት፣ ከተማ ግብርናን ማስፋፋትና ማጠናከር፣ ጤንነቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብርና ምርትና አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ እዲቀርብ ማድረግ ላይ ሰፊ ሥራ መሰራቱ ገልፀዋል።
አያይዘውም ከቁልፍ ተግባራት አኳያ አስተዳደራዊ የሆኑ በርካታ ሥራዎች የተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሁንና ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር በቁልፍ ተግባርም ሆነ በዐብይ ተግባር የአፈፃፀም ክፍተቶች መኖራቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አንስተው የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
ም/ኮማሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ አርሶ አደሩን መልሶ ከማቋቋምና ከማልማት ጋር በተያያዘ ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፤ ይሁንና መረጃ አደራጅቶ ከመያዝ አንፃር፣ መብት ፈጠራ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ በተለይ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር መቀናጀት እና ትኩረት ሰጥቶ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።
ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ በርካታ ሥራዎች በግማሽ ዓመቱ የተሰሩ መሆኑን ገልፀው ነገር ግን ነባርና አዲስ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን መረጃ ጥርት ባለ መንገድ በማደራጀት ዕቅድና ሪፖርታችንን ከላይ እስከታች በተናበበ መንገድ መያዝ አለብን ብለዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ የማዕከል፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮችም የ6 ወራት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ በጥንካሬና በክፍተት አለ ያሉትን ሃሳብ አንስተዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ መደበኛ እና የሌማት ቱርፋት ሥራዎችን አቀናጅቶ መምራት፣ ዕቅድን ከሪፖርት ጋር አናቦ መሬት ላይ ሕይወት እንዲኖረው ማድረግ፣ መረጃን በጥራት ማደራጀት፣ ቁልፍና ዐበይት ተግባራትን አጣጥሞ መሥራ፣ በመደመር መንግስት የተቀመጡ 6ቱን ግቦች ወደራሳችን ስቦ በዕቅድ መምራት፣ ቅንጅታዊ ሥራዎችን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመናበብ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠንከር ያለ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments