ለሚፈጠሩ  ብልሹ  አሰራሮች ማስተካከያ የመፍትሄ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ለሚፈጠሩ  ብልሹ  አሰራሮች ማስተካከያ የመፍትሄ እርምጃ  መወሰድ አለበት፡፡

ለሚፈጠሩ  ብልሹ  አሰራሮች ማስተካከያ የመፍትሄ እርምጃ  መወሰድ አለበት፡፡
  
አዲስ አበባ፤ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም

በ2018 በጀት  ዓመት  የ2ኛ ሩብ ዓመት የኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ  አሰራር   ላይ በየደረጃው የተሰሩ ስራዎችን ከውስጥ  ባለድርሻዎቻችን ጋር ባደረግነው ትስስር መሰረት የእቅድ አፈጻጸም የጋራ ውይይት ተደረገ፡፡

ውይይቱ ያስፈለገበት ዋና አላማ ስራዎቻችን በተናጠልም ሆነ በቡድን ስንሰራ የቆየን ቢሆንም ህግና መመሪያን  እያስጠብቀን የመራንበትን አግባብ ለመገምገም ነው(የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መርጋ ጢጣ)፡፡

የተለያዩ  ተግባራትን በአግባብም ሆነ ያለ አግባብ  የተሰሩ ስራዎችን በሱፐርቪዥን አማካኝነት ተዘዋውረን  ማየትና ማረጋገጥ  እንደሚያስፈልግና ብልሹ አሰራሮች ላይ ማስተካከያ የመፍትሄ እርምጃ ወስዶ  ድጋፍና ክትትሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ዳይሬክተሮቹ ተናግረዋል፡፡

 በመሆኑም ከተቋማችን ባህሪ አንጻር የኬጅ፣የዶሮ  ጫጩት  እና  መኖ ስርጭትን   በተመለከተ  ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እየተደረገ መሆንንም  በትኩረት መከታተል እንደሚገባ  ተብራርቷል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments