ከተማ ግብርና እያመጣ ያለውን ውጤት በጥናት ማረ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ከተማ ግብርና እያመጣ ያለውን ውጤት በጥናት ማረጋገጥ ይገባል።

ከተማ ግብርና እያመጣ ያለውን ውጤት በጥናት ማረጋገጥ ይገባል።


አዲስ አበባ፤ ጥር 04 ቀን 2018 ዓ.ም


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ ከመጡ ምሁራን ጋር በመተባበር ከተማ ግብርና እያመጣ ያለውን ውጤት በጥናት  ለማረጋገጥ የመነሻ  ፕሮፖዛል  ቀርቦ የጋራ ውይይት ተደርጓል፡፡ 
የመነሻ ፕሮፖዛሉን ያቀረቡት ዶ/ር መስከረም ዜጎች በሁሉም ዘርፍ ተሰማርተው የሥርዓተ-ምግብ አቅርቦታቸውን በማሻሻል የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ ከተማ ግብርና አዲስ አበባ ላይ በር ከፍቷል ብለዋል፡፡ 
ዋና ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ የዳሰሳ ጥናቱ እንደ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም የሚጠቅም እንደሆነ አንስተው ከተማ ግብርና ከእድሜ አንጻር የቆ ቢሆንም የከተማው  ህዝብ  የምግብ ዋስትናውን ራሱ እንዲያረጋግጥ የበለጠ ትኩረት የተሰጠው በሌማት ትሩፋት  ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ 
ም/ኮ ኮሚሽነር መሀመድ ልጋኒ  የሌማት ትሩፋት ሕይወት  የዘራበት  በለውጡ ማግስት እንደሆነና ጥናቱ ተቋሙ ላይ ብቻ የሚቀር ሳሆን እንደሀገር ብዙ ችግሮችን የሚፈታ ሊሆን እንደሚችል አንስተዋል፡፡
ም/ኮ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የጥናት ቡድኑ የተደራጀ ፕሮፖዛል ማዘጋጀቱን አድንቀው   ከተማው በከተማ ግብርና ዙሪያ ያለበትን ደረጃ በትክክል ያመላከተ ጥናት ተሰርቶ እንደምናየው እምነቴ ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም የሌማት ትሩፋት ዋና ትኩረቱ እንስሳት እርባታ ላይ በመሆኑ ሳምፕል አወሳሰዱ ላይ ቢታሰብበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የውሃና የመሬት ጥበት ችግር ከተማው ላይ ቢኖርም ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም  ማምረት እንደሚቻል ጅሞሮች አሉ፤ ነገር ግን ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የጥናት ቡድኑ አመላክቷል፡፡ 
ጥናቱ ብሎክን መሰረት ያደረገ እና እንስሳት እርባታው ላይ ትኩረት ያደረገ ቢሆን ችግሮቻችን ለመፍታት  የበለጠ ጤታማ ይሆናል ዶ/ር ደጀኔ ጌታቸው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments