ተረጂነትና ልመናን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎች...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ተረጂነትና ልመናን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

ተረጂነትና ልመናን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡

አዲስ አበባ፤5/5/2018 ዓ.ም 



አስተዳደሩ በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ በሚል መርህ 4ኛ ዓመት 2ኛ ዙር በከተማ ግብርና ሌማት ትሩፋት ዘርፍ ለሚሰማሩ 200 የቤተሰብ ኢንተርፕራይዞች እና ከ900 በላይ ለዘርፉ አንቀሳቃሾች ዘመናዊ የዶሮ ኬጂ፣ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችንና መኖ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አሰራጭቷል። 

በመርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣  የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና  ተገኝተዋል።

የካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ተረጂነትና ልመናን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው እንደ ክፍለ ከተማም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና በመስራት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለትም 150 ባለ 100፣ 50 ባለ 50 ኬጂዎችና ዶሮዎች እንዲሁም ለ3 ወር የሚበቃ የዶሮ መኖ ለ200 ኢንተርፕራይዞች እና 900 አንቀሳቃሾች ማሰራጨት መቻሉን አንስተው የተጀመሩ ግቦችን በማሳካት የየካን ብልፅግና ለማረጋገጥ በጋራ እንስራለን ብለዋል። 
በክፍለ ከተማው በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ በሚል መርህ የተጀመሩ ሰፋፊ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመድረኩ ተመላክተመላክቷል

ምንጭ፡-የካ ክፍለከተማ ኮሙኒኬሽን


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments