በ6ወራት እቅድ አፈፃፀም የታዩትን ጠንካራ ውጤቶ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

በ6ወራት እቅድ አፈፃፀም የታዩትን ጠንካራ ውጤቶች ማስቀጠልና ክፍተቶችን መሙላት ወሳኝ ይሆናል፡፡

ዜና ትንታኔ

በ6ወራት እቅድ አፈፃፀም የታዩትን ጠንካራ ውጤቶች ማስቀጠልና ክፍተቶችን መሙላት ወሳኝ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ፡-ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

ለአርሶ አደሮች ስልጠና በመስጠት፣ የልማት ተነሺዎችን በማደራጀት፣ የፋይናንስ፣ የቁሳቁስና ማሽነሪ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ በእርሻ ሥራ ላይ ለተሰማሩት በከተማ ግብርና እና በሌሎች ልማቶች ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ በማድረግ ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ሌላው በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተደራጁ ነባር ማህበራትን የገበያ ትስስር በመፍጠር ከ100% በላይ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ ወደ ኢቨስትመንት እንዲሸጋገሩ እና የኢኮኖሚ አቅማቸው እንዲያድግ ተደርጓል፡፡

ከእንስሳት ሃብት ልማት የስራ እንቅስቃሴ አንፃር በቤተሰብ ፍጆታ፣ በፋሚሊ ቢዝነስ፣ በእንስሳት እርባታ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ነባርን በማስቀጠል፣ በእንስሳት ጤና ጥበቃ በክትባትና በህክምና፣ የውሻ እብደት በሽታን በመከላከል ረገድ የተሰራው ሥራ ከ100% በላይ ውጤት የተገኘበት ነበር፡፡
በሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል ቴክኖሎጂን በማላመድ፣ ችግኞችን በማልማትና በማሰራጨት፣ ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን ቨበመስጠት የተመዘገበው ውጤት በ6 ወራቱ የታየ ጠንካራ ጎን ቢሆንም ማዕከሉን የበለጠ ማዘመን ቀሪ ተግባር ይሆናል፡፡

ከከተማ ግብርና ስራ አፈፃፀም አንፃር በዘላቂ የኑሮ ዘዴ ማሻሻያ ፓኬጆች ተጠቃሚ ለማድረግ ከታቀደው እቅድ 100% በላይ ተፈፃሚ የተደረገ ሲሆን በእጽዋት ሃብት ልማት የተሰራው ሥራም እጅግ በጣም አበረታች ነበር፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የግብርና ምርት ዕድገትን ከማሻሻል አንፃር በስድስት ወር የተገኘውን ምርት በተመለከተ 50,540 ቶን ታቅዶ 61,980.60 /123%/ቶን ማምረት ከማስቻሉ ባሻገር አርሶ አደሩ በንጥረ ነገር የበለፀገ ስርዓተ ምግብ ተግባራዊ እንዲያደርግና በንጥረ ነገር ይዘቱ የበለፀገና      የተቀናጀ የግብርና ምርት ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የግብርና ምርትና ግብዓት ጥራት፣ ኃይጅንና ደህንነት ከማስጠበቅ አንፃር በሦስቱ ቄራዎች ላይ የተሰራው የሥጋ ምርመራ ሥራ፣ የብቃት ማረጋገጥና የቁጥጥር ሥራ፣ ህገወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን የመቆጣጠርና ህገወጦች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባራት በከፍተኛ ደረጃ ውጤት የተመዘገበባቸው ናቸው፡፡

ከሰርቶ ማሳያና ግብዓት ብዜት ማዕከል እና ከሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ተግባራት በ6 ወራቱ የሥራ አፈፃፀም የተሰበሰበው የውስጥ ገቢ መጠንም ከታቀደው በላይ ነው፡፡
በአስተዳደር ዘርፍ ቱክኖሎጂን ከመጠቀም አንፃር፣ በጀትን በዕቅድ ከማስተዳደር አንፃር፣ በክፍያና የፋይናንስ ሥራ አፈፃፀም አኳያ፣ በኦዲት ሥራዎችን ከመከታተል፣ ግብዓት ከማሟሟላት፣ አገልግሎት አሰጣጥን ከማዘመንና የሪፎርም ሥራዎችን ከማጠናከር አኳያ የተሰራው ሥራ ቀላል የማይባል ነው፡፡

የሰው ኃይል ሥምሪትንም በተመለከተ ሰራተኞችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ምጥጥን በመስራት የተቋሙ ዓላማ እንዲሳካ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፤ የክትትል እና የአቅም ግንባታ ነሥራዎችም ተሰርተዋል፡፡ 

ቅሬታና አቤቱታዎችን በመቀበል ፈጣን ምላሽ የመነስጠት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከደስክ እስከ መስክ በመንቀሳቀስ የመፍታት፣ የህግ ምክርና ድጋፍ የመስጠት ሥራም በግማሽ ዓመቱ በጥሩ ሁኔታ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ከኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ስራ ጋር ተያይዞ የመረጃ ሽፋንና ጥራትን በማሳደግ የከተማው ነዋሪ በኮሚሽኑ የሚሰጠውን አገልግሎት በተገቢው ተገንዝቦ ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰራው ሥራ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

ከአዲስ ሚዲያ ኔቶርክ ጋር ውል በመፈፀም በራዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በአዲስ ልሳን ጋዜጣ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን መሰራቱ፣ በህትመት ሚዲያ በማህበራዊ ሚዲያ፣ ከግልና ከመንግስት የሚዲያ ተቋማት ጋር በመሆን በአጋርነት የተሰራው ሥራ ፋይዳው ቀላል የማይባል ነበር፡፡
 
                         ዜናውን ያዘጋጀችው ባለሙያ፡- መሰረት መኮንን
                                                   ጥር 2018 ዓ.ም
                                                    አዲስ አበባ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments