የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሌማት ትሩፋት ዘርፍ ያስመዘገበው ውጤት የሚመሰገን መሆኑ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሌማት ትሩፋት ዘርፍ ያስመዘገበው ውጤት የሚመሰገን መሆኑ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ፤ ጥር 07 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከ1,200 በላይ ለሆኑ በ11ዱም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎች የግብዓት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ኮሚሽኑ 240 ኬጂ በቤተሰብ ለ1,200 ተጠቃሚዎች፣ 240 ኩንታል የሦስት ወር የዶሮ መኖ፣ ከ12,000 በላይ እንቁላል ጣይ ዶሮዎች፣ 68 የውሃ ፓምፕ ለአርሶ አደሮች እና 70 የውሃ ማጠጫ ለሴት ሞዴል አርሶ አደሮች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የሌማት ትሩፋት የንቅናቄ ፕሮግራም በሀገር አቀፍ እንዲሁም በከተማችን አዲስ አበባ ደረጃ በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና ማር ምርቶች ላይ መሰረታዊ ለውጥ በማምጣት በቤተሰብ ደረጃ የተመጣጠነ የምግብ ስርዓትን ተግባራዊ ከማድረግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ህልም የሰነቀ መሆኑን በግብርና ሚንስቴር የእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚንስቴር ዴታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሣ ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ፕሮግራሙ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥና ድህነትን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲሁም የኑሮ ዉድነትን ለማቃለልና ለዜጎች የገቢ ምንጭ ለመፍጠር ሚናው የጎላ በመሆኑ በአዲስ አበባ ከተማ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የተጠሪ ተቋማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ በበኩላቸው አዲስ አበባ ከተማ ላይ ግብርና ከለውጡ በፊት ቢኖርም እዚህ ግባ የሚባል ስራ አልነበረውም፤ ዛሬ ግን አዲስ አበባ በምግብ ራሷን እየቻለች ትገኛለች ብለዋል፡፡
አያይዘውም በሌማት ትሩፋት ፕሮግራም ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በመጠቀም የእንስሳት ሀብት ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የቤተሰብ ብልፅግናን ከማረጋገጥ ጀምሮ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር፤ ገበያን ማረጋጋት እና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ሥራ በስፋት መሰራቱን ገልፀዋል፡፡
የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የሌማት ቱሩፋት ፕሮግራም በ2015 ዓ.ም እንደ ሀገር እንዲሁም በከተማችን አዲስ አበባ ከተጀመረ በኋላ ለባለፉት ዓመታት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጧል፡፡ አያይዘውም ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በእለቱ የግብዓት ድጋፍ የተደረገላቸው ተጠቃሚዎችም ለተደረገላቸው ድጋፍ ለመንግስት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments