በማዕከሉ የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ተደረገ።
በማዕከሉ የበሽታ ስርጭትን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ተደረገ።
አዲስ አበባ፤ ጥር 07/2018 ዓ.ም
===
ዛሬ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በሌማት ትሩፋት የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የዶሮ፣ የዶሮ ኬጅ፣ መኖ፣ የውሃ ፓምፕና የመድሃኒት መርጫ በማዕከሉ አሠራጭቷል።
ይህንን ተከትሎ በማዕከሉ የግቢ በር አካባቢ ከፍተኛ የህዝብ ፍሰት/Traffic/ ስለነበር የበሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የኬሚካል ርጭት ተደርጓል።
የስነ ህይወት ደህንነት /Biosecurity/ ተግባር በእንስሳት እርባታ ስራ ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠውና ለአፍታም መዘንጋት የሌለበት ተግባር በመሆኑ በከፍተኛ ጥንቃቄ መመራት እንዳለበት የዘርፉ ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
የመረጃ ምንጫችን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments