ሥራዎቻችን አስረጅ (Attachments) ሊኖራቸ...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

ሥራዎቻችን አስረጅ (Attachments) ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ሥራዎቻችን አስረጅ (Attachments) ሊኖራቸው ይገባል፡፡


አዲስ አበባ፤ ጥር 09 ቀን 2018 ዓ.ም



የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የባለፈውን 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም መሰረት በማድረግ የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛው ግማሽ ዓመት ዕቅድ ክለሳን እና የጥር ወር የመጀመሪያው ሳምንት ዕቅድ አፈፃፀምን በጀነራል ካውንስል የጋራ አድርጓል፡፡
ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኔ በ6 ወራት ውስጥ የሰራናቸው ሥራዎች ዕቅድ አፈፃፀም አስረጅ (Attachments) ሊኖራቸው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የ2018 በጀት ዓመት የ2ኛው ግማሽ ዓመት ዕቅድ ክለሳ የመጀመሪያውን መንፈቅ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም መነሻ በማድረግ፣ ከተለያዩ ከሚመለከታቸው አካላት ከድጋፍና ክትትል፣ ከሱፐርቪዥን፣ ከኢንስፔክሽን እንዲሁም ከጉብኝትና ልምድ ልውውጥ የተገኙ መነሻዎችን በመውሰድ ዕቅዱ ተከልሶ በአስቼኳይ ገቢ እንዲሆን የዘርፍ ኃላፊዎች አሳስበዋል፡፡
የጀነራል ካውንስል አባል የሆኑ ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ ሃሳብ አስተያየት ሰጥተው የጋራ አድርገዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments