የከተሜውን ህይወት የከተማ ግብርና ያቀለዋል::
የከተሜውን ህይወት የከተማ ግብርና ያቀለዋል::
አዲስ አበባ፤ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2050 የዓለም ህዝብ ቁጥር 10 ነጥብ 2 ቢሊዮን እንደሚደርስና የምግብ ፍላጎቱ አሁን ካለው በ70 በመቶ ከፍ እንደሚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትንበያ ያመላክታል። ይህም አማራጭ የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ስልቶች እንደሚያስፈልግ ጠቋሚ ነው፡፡ ታድያ የከተማ ግብርና ስራ ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እሙን ነው።
የዓለም ህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የከተሜነት መስፋፋት፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ተፅዕኖዎች እየተባባሱ መምጣት የምግብ ዋስትና ጉዳይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ከሚያስገድዱ ምክንያቶች በቀዳሚነት ተጠቅሰዋል፡፡
ችግሩን ለመቋቋም ከተቀመጡ የመፍትሔ አማራጮች መካከል ደግሞ ዘመናዊ የከተማ ግብርናን ማስፋፋት አንዱ ነው። የከተማ ግብርና ምርትና ምርታማነትን በመጠንም በጥራትም በማሳደግ ኢኮኖሚን ይደጉማል፤ በከተማና በከተማ ዙሪያ የሚኖረውን ህብረተሰብ የስርዓተ-ምግብና የምግብ ዋስትና እንዲሻሻልም ጉልህ አበርክቶ እንዳለው ታምኖበት እየተሰራበት ይገኛል፡፡
ስለሆነም በሀገራችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለከተማ ግብርና ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ምንጭ፡- አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments