የተቀዛቅዘውን የማዕከሉን ሥራ የማነቃቃት ተግባራ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የተቀዛቅዘውን የማዕከሉን ሥራ የማነቃቃት ተግባራት እየተከናወኑ ነው፡፡ ዶ/ር ፀጋ ለማ

አዲስ አበባ፤ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) በማእከሉ ለሥራ እንቅፋት የነበሩ የግንባታና ዲዛይን ሥራዎች እና የውሃ አቅርቦት ችግርን በማስተካከል የተቀዛቀዘውን ሥራ ወደ ነበረበት ለመመለስ ሥራዎች የተጠናቀቁ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የማዕከሉ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) ማዕከሉን ወደነበረበት ለመመለስ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ወደ ተቋሙ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ የኮሚሽኑን ስትራቴጅክ ካውንስል በመያዝ 24 ስዓት እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡ 

በሌላ በኩል አጋጥሞ የነበረውን የውሃ እጥረት እና የጽዳት ሥራ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ፣ መንገዶች ባለስልጣን እና የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ትብብር በማድረጋቸው ችግሩን ለመፍታት ተችሏል ብለዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘውም ማህበራቱ የስራ ፍላጎት ቢኖራቸውም የዶሮ ኬጅው ከደረጃ በታች በመሆኑ ለሥራቸው እንቅፋት ሆኖ የነበረ መሆኑ እና አሁን ላይ አስፈላጊውን ማስተካከያ በማድረግ ለሥራ ዝግጁ የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከውሃ ጋር ተያይዞ የነበረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አሁን ላይ የከርሰ ምድር ውሃ የወጣ መሆኑን ፀጋ ለማ (ዶ/ር) አንስተዋል፡፡

ኃላፊ ማህበራቱ በማዕከሉ ባሉ የመሸጫ ሱቆች እና በሸማች ማህበራት በኩል ግብይት እንዲፈጽሙ በሁለት መንገድ ትስስር የተፈጠረላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሌላው በቀጣይ መጠናቀቅ ያለባቸው የግንባታ ሥራዎች እና ሌሎች የማዕከሉ ሥራዎች በወቅቱ ከተጠናቀቁ ማዕከሉ በቂ የሆነ ምርት ለተጠቃሚዎች ማቅረብ የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments