የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሥራዎችን በተሳለጠ መንገድ ለመምራት አቅም ነው።
የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ሥራዎችን በተሳለጠ መንገድ ለመምራት አቅም ነው።
አዲስ አበባ፤ ጥር 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የኮሚሽኑን የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ገምግሟል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙ የቀረበበት አግባብ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ከቀረበው ሪፖርት በመነሳት ጥንካሬዎችን አጠናክሮ ማስቀጠልና ክፍተቶችን ማረም ከሁሉም ሰራተኞች ይጠበቃል ብለዋል።
አክለውም ዋና ኮሚሽነሩ የከተማ ግብርናችን ቴክኖሎጂ መር መሆን አለበት፤ ከከተማችን ልማት አንፃር የመደመር መንግስት ያስቀመጣቸውን 6 ግቦች በተለይም ከኮሚሽናችን ተግባርና ኃላፊነት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ላይ ልዮ ትኩረት በመስጠት የከተማ ግብርና ምርትን በእጥፍ ማሳደግ እንዲሁም አግሪ ቱሪዝምን እንደ ከተማ ተግባራዊ ማድረግ አለብን ብለዋል።
የሰርተፊኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ ኳራንታይንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ ፀጋ ለማ (ዶ/ር) የከተማዋ ነዋሪ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የግብርና ምርትና ግብዓት ማግኘት እንዲችል በኮሚሽኑ ተዋረዳዊ መዋቅርና በቅንጅት በስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም አሰራር በመዘርጋት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጂት ህገ-ወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን በመቆጣጠርና ተጋላጭ ሆነው ሲገኙም አስተማሪ እርምጃ በመውሰድ ስታንዳርድ የማስጠበቅ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መሐመድ ልጋኒ በዘርፍ በርካታ ሥራዎች የተከናወኑ ቢሆንም የተወሰኑ የሚታዮ ክፍተቶችን ሁሉም ባለሙያ ወደራሱ ወስዶ ማረም ይገባል ብለዋል።
ሌላው በመደመር መንግስት የተቀመጡ 6 ግቦችን ሁሉም ሰራተኞች በሚገባ ተረድተው የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
የኮሚሽኑ ሰራተኞች በ6 ወራቱ ውስጥ የነበሩ ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን አንስተው ክፍተቶች በቀጣይ ሊስተካሉ ይገባል በማለት አንስተዋል።
የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ በሪፖርቱ የተቀመጡና በውይይታችን ያነሳናቸውን ጥንካሬዎችና ክፍተቶች ወደራሳችን ወስደን ክፍተቶቻችንን ፈጥነን ማረም ይገባል ብለዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ተጠያቂነትን በማስፈን፣ ሪፖርት ከባለሙያዎች እንዲነሳ በማድረግ፣ አደረጃጀትን በማጠናከር፣ ለሠራተኞች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የተቋሙን አፈፃፀም ማሻሻል ይገባል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments