የየሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መድረክ፡፡
የየሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መድረክ፡፡
AI የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ማሽኖች የሚያዳብርና የሚያጠና የጥናት መስክ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ጥር 18/5/2018 ዓ.ም
ሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) አንድ ጎራ ውስጥ ያሉ የእውቀት የፅንሰ-ሀሳቦች ስብስብ እና በእነዚያ ጽንሰ-ሀሳቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ይወክላል።
የእውቀት ውክልና እና የእውቀት ምህንድስና የ AI ፕሮግራሞች ጥያቄዎችን በብልህነት እንዲመልሱ እና በገሃዱ ዓለም እውነታዎች ላይ የጊዜና ጉልበት ቅናሽ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል (ፍቅርማርም ይትባረክ የዌብሳይት አድሜንስትሬተር ባለሙያ)።
አቅራቢው አያይዘውም ሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) ከሰዎች ወይም ከእንስሳት ዕውቀት በተቃራኒ የማሽኖች ወይም የሶፍትዌሮች የማሰብ ችሎታ መሆኑን ገልጸዋል።
የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ማሽኖች የሚያዳብርና የሚያጠና የኮምፒውተር ሳይንስ የጥናት መስክ ነው። ሌላው እንደነዚህ ያሉት ማሽኖች ኤአይስ ተብለው እንደሚጠሩ ተብራርቷል።
በተጨማሪም AI ምስሎችንና ድምጾችን፣የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን ፣የቋንቋ ትርጉሞችን እና የአውቶማቲክ ስራዎችን ወ.ዘ.ተ ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ በቀረበው ሰነድ ላይ ተካቷል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments