የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ተቋምን ለመገንባት  ት...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ተቋምን ለመገንባት  ትልቁን ሚና ይጫወታሉ፡፡

የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ተቋምን ለመገንባት  ትልቁን ሚና ይጫወታሉ፡፡

አዲስ አበባ፤ጥር 18/5/2018 ዓ.ም

የህዝብ አስተያየት ቅኝት ዳሰሳ እና የሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ሥራ የዳሰሳ ጥናት ግኝቶች እና ምክረ-ሃሳብ ለኮሚሽኑ ጠቅላላ ሰራተኛ እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ግኝት እንደሚጠቁመው ተገልጋዮች ለተሰጣቸው አገልግሎት አስተያየት የመስጠት ልምዳቸው እና አገልግሎት የሰጠው አካልም ስለሰጠው አገልግሎት አስተያየት የመቀበል ልምዱ ዝቅተኛ መሆኑ ነው፡፡

በአዎንታና በአሉታ የተሰጡ የህዝብ አስተያየቶችን ተንትኖ የዕቅድ አካል አድርጎ መስራትም ሌላው በጥናቱ የተገኘ ውስንነት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡

ሌላው ከሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራዎች ጋር በተያያዘ በተደረገ ዳሰሳ ጥናት የኮሚሽኑ አጠቃላይ ሰራተኞች ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለው ተሳትፎ ውስንነት ያለበት ቢሆንም ተገልጋይ ለሚሰጠው አስተያየትና ለሚያነሳቸው ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ልምድ እየተሻሻለ የመጣ መሆኑ ታይቷል፡፡

ከተደረገው ዳሰሳ ጥናት የተገኘው ግኝት እንደሚያሳየው አማራጭ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ፕላት ፎርሞችን መጠቀም፣ ምርጥ ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት፣ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች እስከታችኛው መዋቅር ያሉት በንቃት መሳተፍ፣ ተገልጋይ አስተያየት የሚሰጥባቸውን መንገዶች ማስፋትና ለተሰጡ አስተያየቶች ፈጣን ምላሽ መስጠት ተጠናክሮ ሊሰራባቸው የሚገቡ ጉዳዮች መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments